Fana: At a Speed of Life!

የ”ጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ” ንቅናቄ በአማራ ክልል ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የ”ጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ” ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ አረጋ ከበደ÷ ጽዱ አካባቢና ጽዱ ጤና ተቋማት ለመፍጠር የተጀመረው ተግባር አመራሩና ባለሙያው በውል ተገንዝቦ ማህበረሰቡን በማሳተፍ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በርካታ ለውጦች የተመዘገቡበት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በተለያዩ ምክንያቶች እየተቀዛቀዘ መምጣቱን አንስተዋል፡፡

በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የማህበረሰቡ ጤና እንዲጠበቅ መትጋት ያስፈልጋል ያሉት አቶ አረጋ÷ የተጀመረውን ተግባር ዘላቂነት አረጋግጦ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተግባሩን በቁርጠኝነት መተግበር፣ መግባባት መፍጠርና ቅንጅታዊ አሰራር በማጎልበት ጽዱ አካባቢና ጽዱ ጤና ተቋም ለመፍጠር በትኩረት እንዲመሩ አስገንዝበዋል።

ለዕቅዱ ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውንም የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.