Fana: At a Speed of Life!

በሕንድና ባንግላዲሽ የተከሰተ አውሎ ነፋስ የ9 ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) በሕንድ እና ባንግላዲሽ “ሬማል” የተሰኘ ከባድ አውሎ ነፋስ ባስከተለው አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ1 ሚሊየን የሚልቁ ተፈናቀሉ፡፡
 
አውሎ ነፋሱ በባንግላዲሽ ሞንግላ ወደብ እንዲሁም በሕንድ ሳጋር ደሴቶች አቅራቢያ መከሰቱን የሕንድ የአየር ትንበያ ክፍል አስታውቋል፡፡
 
በሠዓት እስከ 135 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘገው አውሎ ነፋስ÷ በአካባቢው አቆጣጠር ትናንት ምሽት 3 ሠዓት አካባቢ መከሰቱና ለአምስት ሠዓታት መቆየቱ ተመላክቷል፡፡
 
ክስተቱን ተከትሎም በባንግላዲሽ ባሪሻል፣ ሳትኪራ፣ ፓቱካሊ፣ ቦላ እና ቻቶግራም አካባቢዎች የሰባት ሰዎች ሕይወት ሲቀጠፍ÷ በሕንድ ምዕራብ ቤንጋል ደግሞ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
 
የአውሎ ነፋሱን መከሰት ተከትሎም የሕንድ ኮልካታ አየር መንገድ 50 የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ በረራዎች መሰረዙ ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.