Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ኦብነግ፣ ምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር፣ ነፃነትና እኩልነት፣ ህብረት ለዴሞክራሲና ለነፃነት እንዲሁም ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲዎች ተገኝተዋል።

ፓርቲዎቹ በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች፣ በህግ የበላይነት መከበር፣ በክልሉ ሰላማዊና መተማመን ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ እንቅስቃሴን መከተል እንዲሁም የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በክልሉ ያለውን ሰላም ለማጠናከር እና በተገኘው ሰላም መሠረት ልማት ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መስማማታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.