Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኡሞድ ሰላምን በማስፈን የልማት ሥራን ለማከናወን በሚደረገው ጥረት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲረባረቡ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም በማስፈን የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲረባረቡ ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ጠየቁ፡፡

አቶ ኡሞድ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ክልላዊ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ መክረዋል፡፡

በምክክራቸውም በጋምቤላ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የተሻለ ውጤት የሚታይባቸው በመሆኑ ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች እንዲስፋፉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡

እንዲሁም በጋምቤላ ክልል ያለው የፀጥታ ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ÷ አሁን ላይ ዘረፋና ስርቆት በመስፋፋቱ ዜጎች ለጉዳት ተዳርገዋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

አቶ ኡሞድ በሰጡት ማብራሪያ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ መንግሥት በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታውቀው÷ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲረባረቡ ጠይቀዋል፡፡

መንግሥት የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ የክልሉን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረትም የድርሻቸውን እንደሚወጡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቱ አረጋግጠዋል፡፡

ከውይይቱ ጎን ለጎንም በጋምቤላ ከተማ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.