Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ዐውደ-ርዕይና ሲምፖዚየም ከፊታችን ግንቦት 22 ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ዐውደ-ርዕይ እና ሲምፖዚም ከግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተመላከተ፡፡

“ኢትዮጵያን እንገንባ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው የቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ዐውደ-ርዕይ እና ሲምፖዚየም የግንባታ ኢንዱስትሪውን ልማት፣ ዕድገት እና ስኬት ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል መሆኑን የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል፡፡

ተግዳሮቶችን ዐውቆ ችግሮችን ወደ ዕድል ለመቀየር፣ የፋይናንስ፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚረዳም አስረድተዋል፡፡

ከግንባታ ማዘመን እስከ አገልግሎት ያለውን ሂደት በማሣደግ ስማርት ሲቲን ለመገንባት የሚያስችል ልምድና ዕውቀት እንደሚገኝበት መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የዓለም አቀፉ ዲኤምጂ ኢቨንትስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ቤን ግሪንሽ በበኩላቸው ዐውደ-ርዕይ እና ሲምፖዚየሙ በኢትዮጵያ መካሄዱ ለግንባታው ዘርፍ ዕድገት የገበያ ዕድል እንደሚያመጣ ገልጸው÷ ይህም ዘላቂ የልማት ዕድገትን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.