Fana: At a Speed of Life!

3 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ አስር ወራት 3 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሃና አርያስላሴ ገለጹ።

ሃና አርያስላሴ ÷ መንግስት ኢትዮጵያን ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም አዳዲስ ሴክተሮችን፣ የወጪና ገቢ ንግድ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ዝግ የነበሩ ሴክተሮች ለኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ደግሞ ከተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለውጭ ባለሀብቶች የሚያስተዋውቁ መረሃ-ግብሮችን በማስተዋወቅ ረገድ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

በዚህም ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማምረቻ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በቱሪዝም፣ በጤና እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች ላይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋዕለ ነዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሃብቶች የምትሰጠውን ማበረታቻ እያስተዋወቀች ትገኛለች ብለዋል።

በ2016 በጀት ዓመት ኮሚሽኑ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እቅድ ይዞ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው በዚህም በበጀት ዓመቱ 10 ወራት 3 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

ቻይና ፣ ኔዘርላንድ፣ ቱርክ እና ህንድ በኢትዮጵያ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከሚሳተፉ ዋና ዋና ሀገራት መካከል መሆናቸውና የቻይና ኩባንያዎች ደግሞ ቀዳሚውን ደረጃ እንደሚይዙ ነው የጠቀሱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.