Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ሱቱሜ አሰፋ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድንን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ስብስብ ውስጥ ተካተች፡፡

አትሌቷ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ግንቦት 8 በፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በማራቶን የሚወክሉ አትሌቶችን ስም ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ሳትካተት መቅረቷ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ አትሌቷ ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቅሬታ አቅርባለች።

በዚህም መሰረት አትሌቷ ያቀረበችው ቅሬታ ተቀባይነት በማግኘቱ በዛሬው እለት የፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያውያን የሚወክሉ አትሌቶች ወደሚገኙበት ሆቴል እንድትቀላቀል ተወስኗል።

ሱቱሜ አሰፋ በ2024ቱ የቶኪዮ ማራቶን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በመግባት ማሸነፋ ይታወሳል።

ከዚህ በተጨማሪ በህንድ ኮልካታ ግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.