Fana: At a Speed of Life!

ጣልያን ለኢትዮጵያ ቅርስ እድሳቶችና ለቱሪዝም ልማት ስራ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች ለሚከናወኑ የቅርስ እድሳቶች እና የቱሪዝም ልማት ስራዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በኢትዮጵያ የጣልያን ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከጣልያን አምባሳደር ኦግስቲኖ ፔልሲ ጋር በቱሪዝም ዘርፍ ከጣልያን መንግስት ጋር በትብብር ስለሚከናወኑ ስራዎች መክረዋል፡፡

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚከናወኑ የቅርስ እድሳቶች እና የቱሪዝም ልማት ስራዎች የጣሊያን መንግስት የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡

በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፍ የሰው ኃይል ልማት እና ስልጠና ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.