Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ተከትሎ  43 የአፍሪካ አገራት ድንበሮቻቸውን ሙሉ በሙሉ ዘጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2012 ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአፍሪካ  በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ  43 የአፍሪካ አገራት ድንበሮቻቸውን ሙሉ በሙሉ ዘግተዋል።

በአህጉሪቱ በሽታው በፍጥነት  መስፋፋት ላይ ሲሆን እስካሁን ከ 225 ሺህ 105 በላይ  ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው  ተነግሯል።

በበሽታውከተያዙት በተጨማሪ በተከሰተው ወረርሽኝ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 40 የደረሰ ሲሆን ሌሎች 102 ሺህ 846 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ማገገማቸውን በአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እናመቆጣጠሪያ ማእከል (አፍሪካ ሲዲሲ) የወቅቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለሆነም ስርጭቱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሀገራቱ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

በዚህም በተጨማሪም 54 የአፍሪካ አገራት የተገደበ ሕዝባዊ ስብሰባን  ተግባራወዊ ያደረጉ ሲሆን ÷ 38 የሚሆኑት አገራት በመላው አገሪቱ የትምህርት ተቋማትን  ዘግተዋል ።

43 ሀገራት ድንበራተቸውን ሙሉ በሙሉ የዘጉ ሲሆን  ከዚህ በተጨማሪም 35ቱ ሀገሮች  የምሽት የሰዓት እላፊ ማወጃቸውን የአፍሪካ ሲዲሲ  ገልጿል።

ሰባት አገራት  ዓለም አቀፍ የአየር ትራፊክ ን የዘጉ ሲሆን ÷ሁለት ሀገራት ደግሞ ለተወሰኑ አገሮች ከዚያ የሚመጡ እና ወደ እነሱ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ  የጉዞ ገደቦችን  ጥለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ አገሮች  የጭነት እና የድንገተኛ ጊዜ ትራንስፖርት እንዲገቡና እንዲወጡ የሚፈቅዱ መሆኑ ተነግሯል።

ከዚያም ባለፈ በአህጉሪቱ የኮቪድን ስርጭትን ለመቆጣጠር  ÷18 ያህል አገራት የጅምላ ማጣሪያ እና ምርመራ ማካሄድ የጀመሩ ሲሆን 41 አገራት  ህዝባቸው የፊት ጭንብል  እንዲያደርግ አስገዳጅ ህግ አውጥተዋል።

በአህጉሪቱ ደቡብ አፍሪካ 65ሺህ 736  ዜጎቿ በኮቪድ የተያዙ ሲሆን ÷1ሺህ 423 ሰዎች  ደግሞ በበሽታው ለህልፈት መዳረጋቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ አስታውቋል ።

ይሁን እንጂ በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በበሽታው በተያዙ ሰዎች እና በመሟቾች ቁጥር  ቀዳሚ መሆኑ ተነግሯል።

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ልዩ የጤና አጠባበቅ ኮሚሽን በበኩሉ÷ በአፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ በወረርሽኙ ከተጠቁት ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ፣ ግብፅ ፣ ሞሮኮ ፣ ጅቡቲ ፣ ናይጄሪያ እና አልጄሪያ ይገኙበታል ብሏል ፡፡

ግብፅ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 1ሺህ 677  በበሽታው አዲስ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ  በአጠቃላይ በአገሪቱ  በኮቪድ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 42 ሺህ 980  እንዲያሻቅብ  ማድረጉን የግብፅ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ቃል አቀባይ  አስታውቀዋል ፡፡

ከዚያም ባለፈ በግብጽ በአንድ ቀን 62 ጭማሪ ሞት  ማስመዝገቧን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ   ካሃሊድ መግሃድ ገልጸዋል ፡፡

ምንጭ፡-ዴይሊ ኔሽን

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.