Fana: At a Speed of Life!

የጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ ንቅናቄ በሃዋሳ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሃዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

ንቅናቄውን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስጀምረዋል፡፡

አቶ ደስታ ÷ ጽዱ አካባቢ ላይ መኖር ትልቅ ውበት እና እድገትን ይጨምራል፤ አከባቢያችን ማስዋብ ከቻልን የሀገራችንን ከፍታ እናረጋግጣለን ብለዋል።

ሃዋሳን ለሩሮና ኢንቨስትመንት ምቹ እንድትሆን በንቅናቄው ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃ ቤቶችን በመገንባትና በመንከባከብ የኢትየጵያን እድገት ለማጉላት እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አፈ-ጉባዔ አገኘሁ በበኩላቸው÷ሃዋሳ ከተማን የበለጠ ለማስዋብ ደረጃውን የጠበቁ መጸዳጃ ቤቶች ያስፈልጋሉ፤ ይህን ማድረግ ከተቻለ የከተሞች ከፍታና ውብ አከባቢን መፍጠር ይቻላል ብለዋል።

በሃዋሳ ከተማ ለሚሰራው መጸዳጃ ቤት ንቅናቄም አፈ-ጉባዔ አገኘሁ 10 ሺህ ብር በመስጠት እና በፌደሬሽን ምክር ቤት ደግሞ 100 ሺህ ብር ቃል በመግባት ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በተደረገ ንቅናቄ በደመወዝ ቃል የገቡትን ጨምሮ 43 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.