Fana: At a Speed of Life!

ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም ከተረጂነት ለመላቀቅ መረባረብ ይገባል-አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም ከተረጂነት ለመላቀቅ መረባረብ ይገባል ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

በሀረሪ ክልል “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር” በሚል መሪ ሀሳብ በክልል አቀፍ ደረጃ ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ  ላይ ያተኮረ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንዳሉት÷  እንደ ሀገር ከተረጂነት እና ከልመና መላቀቅ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ነው።

ከተረጂነት አስተሳሰብ ሳይላቀቁ ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ክብርን በሙሉዕነት መጎናፀፍ  አይቻለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷እንደ ሀገርና ክልል  እምቅ ሀብቶችን በአግባቡ  በመጠቀም የተረጂዎችን ቁጥር  መቀነስ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በተለይም አመራሩ ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም የተረጂነትን አስከፊነት እና ጉዳት ከሀገር ሉዓላዊነትና ሁለንተናዊ ብልፅግና አኳያ በጥልቅ በመረዳት ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት መንቀሳቀስ እንደሚገባውም ጠቁመዋል።

ለዚህም ብቸኛው መፍትሄ ምርታማነትን በሁሉም ደረጃ ማሳደግ መቻል  እና የስራ እድልን በስፋት መፍጠር ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.