Fana: At a Speed of Life!

ከወርቅ ወጪ ንግድ 274 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 274 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው የማዕድን ሚኒስቴርን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያዳመጠ ነው፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)÷ በበጀት ዓመቱ የወጪ ማዕድናት ምርትን በስፋትና በጥራት በማምረት ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግ ላይ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

በኩባንያዎች 2 ነጥብ 414 ቶን እንዲሁም በባህላዊ 0 ነጥብ 609 ቶን በአጠቃላይ 3 ነጥብ 023 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን አንስተዋል፡፡

በዚህም 274 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 83 በመቶ ብልጫ እንዳለው መናገራቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.