Fana: At a Speed of Life!

ብሔር-ተኝነት የተሰኘ መፅሃፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ በሆኑት ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) የተፃፈ ብሔር-ተኝነት የተሰኘ መፅሃፍ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተመረቀ።

ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ስለመፅሃፋቸው ሲያስረዱ፥ መፅሃፉ ከዝግጅት እስከ ህትመት አምስት ዓመታትን እንደወሰደ ተናግረዋል።

ከመፅሃፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በሁሉም ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳድሮች ለወጣት ልማት ፕሮጀክቶች ይውላል ብለዋል።

መፅሃፉ በ15 ምዕራፎችና በ5 ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን፥ የብሔር-ተኝነት ፅንሠ ሃሳብን በጥልቀት ከመተንተን ባለፈ ፅንሰ ሃሳቡን ቀላልና ተጨባጭ እንዲሆን አድርጎ ተዘጋጅቷል ነው የተባለው።

መፅሃፉ በተለዋዋጭ የዓለም ፖለቲካዊ ውስጥ ብሄር-ተኝነት ቋሚ ርዕዮት ሁኖ ስለመቀጠሉም ያስረዳል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር በዚሁ ጊዜ፥ መፅሃፉ ለአሁናዊ እንዲሁም ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ጠቃሚ ሰነድ ነው ብለዋል።

አክለውም፥ በሀገራችን የብሔር-ተኝነት የተሳሳተ ትርጓሜን ማረም የሚችል በጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ሰነድ ሆኖ ማግኘታቸውንም ገልጸዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘው ተሻገር፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድር፣ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች፣ ደራሲያንና ጋዜጠኞች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመራዖል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.