Fana: At a Speed of Life!

ተመድ ኢትዮጵያ በነዳጅ የዲጅታል ግብይት እየሰራች ያለውን ስራ አደነቀ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድ ኮንፈርንስና ልማት ድርጅት የአፍሪካ ተወካይ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የንግድ ዘርፉን ለመደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ተወካይዋ ÷ኢትዮጵያ በንግዱ ዘርፍ በተለይም የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎትና በነዳጅ የዲጅታል ግብይት እየሰራች ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡

ተቋማቸውም የወጪ ንግድ ፕሮሞሽንና ኢንቨስትመንትን እንዲሁም ኢ-ኮሜርስን በቴክኒክና ፋይናንስ መደገፍ እንደሚፈልም መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በበኩላቸው÷ ድርጅቱ ቀደም ባሉት ጊዜያት የዘርፉን እድገት ለማፋጠንና ለማዘመን የቴክኒክና ፋይናንስ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር አስታውሰው ፤ ወደፊትም የተጀመረውን የአውቶሜሽን ስራ የበለጠ ለማጠናከር ድጋፉ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በወጪ ንግድ ፕሮሞሽንና የምርቶችን የመዳረሻ ሀገራት ከማስፋትና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የሚኖረንን የንግድ ትስስር ለማጠናከር እየሰራን ላለው ስራ የተመድ የንግድ ኮንፈርንስና ልማት ድርጅት ድጋፍ አስፈላጊ በመሆኑ አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.