Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቢሳው አቀና

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ መዲናዋ ቢሳው ተጉዟል።

23 ተጫዋቾችን ያካተተው ልዑካን ቡድኑ ከአዲስ አበባ በቶጎ (ሎሜ) አድርጎ ቢሳው ከተማ ዛሬ ምሽት ላይ እንደሚደርስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ወደ ጊኒ ቢሳው ከማምራቱ አስቀድሞ የመጨረሻ የሀገር ቤት ልምምዱን ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ማከናወኑ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.