Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ በፒኬኬ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ በኢራቅ በሚገኘው የኩርድ የሰራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ) ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።

የሃገሪቱ የጦር ጀቶች ትናንት በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኘው የቡድኑ ይዞታ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸማቸው ታውቋል።

የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴርም በተለይም የቡድኑ ጠንካራ ይዞታ እንደሆነ በሚነገርለት ቃንዲል በተባለው አካባቢ ጥቃት መፈጸሙን በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

በአየር ድብደባው ስለደረሰው ጉዳትሚኒስቴሩም ሆነ ቡድኑ ያሉት ነገር የለም።

ሚኒስቴሩ ፒኬኬን ጨምሮ ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች ለቱርክና ህዝቦቿ የደህነነት ስጋት መሆናቸውን ጠቅሷል።

በአብዛኛው በሰሜናዊ ኢራቅ እና በደቡብ ምስራቅ ቱርክ መቀመጫውን ያደረገው ፒኬኬ ነጻ የኩርድ መንግስት ለመመስረት በሚል ከፈረንጆቹ 1984 ጀምሮ በትጥቅ ትግል ላይ ይገኛል።

ከዚያንህ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያም ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል።

ቡድኑ ቱርክን ጨምሮ በአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት አሸባሪ ተብሎም ተፈርጇል።

አንካራ በተለይም ቡድኑ ሰፍሮ በሚገኝባቸው የኢራቅ ተራራማ ስፍራዎች ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን ስትሰነዝር ቆይታለች።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.