Fana: At a Speed of Life!

የዕድሜ ባለጸጋዋ የልጅ እናት ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእድሜ አንጋፋዋ ጣሊያናዊት በ63 ዓመታቸው የልጅ እናት መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ሴት ልጅ በተፈጥሮ ከአርባዎቹ አጋማሽ በኋላ ልጅ የመውለድ ተስፋዋ የጭላንጭል ታክል ናት ይባላል፡፡

ሆኖም አንዳንድ ተፈጥሮና የዓለም ክስተቶች ከማስደነቅም በላይ ሲሆኑ ይታያል፡፡ በጣልያንም የሆነው ይህ ነው፡፡

ፍላቪያ አልቫሮ ይባላሉ፡፡ ልጅ የማግኘት ጉጉታቸው የእድሜ ገደብን ጥሶ በህክምና ጥበብ በመተማመን ወደህክምና ፊታቸውን ያዞራሉ፡፡

በዚህም ከጣልያን በጦርነት ሺህዎች እየረገፉባት ወዳለችው ዩክሬን በማቅናት የመካንነት ህክምናቸውን ይጀምራሉ፡፡

ህክምናውን ካደረጉ በኋላም በብዙዎች ልጅ ለመውለድ የተሟጠጠ ተስፋ እንደሆነ በሚታመንበት እድሜ ላይ የልጅ እናት ሊሆኑ ግድ ሆነ፡፡ ትንሹ ሰባስቲያንም ተወለደ፡፡

ሃኪሟም ‘’ግትር ሴት ናት’’ ሲሉ የገለጿቸው እናት የልጅ ፍቅራቸውን ለማስታገስ የሄዱበት እርቀት በጣልያን ‘’የእድሜ ባለጸጋዋ እናት’’ እስከመባል አድርሷቸዋል፡፡

ልጃቸው ሰባስትያንም በጥሩ ጤንነት እንደሚገኝ የዘገበው ዴይሊ ሜይል ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.