Fana: At a Speed of Life!

የተግባቡ እና የተዋቡ የግንባታ መልኮች አዲስ አበባን እየቀየሯት ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተግባቡ እና የተዋቡ የግንባታ መልኮች አዲስ አበባን እየቀየሯት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

“ሰፋፊ ጎዳናዎች፣ ምቹ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶች፣ አረንጓዴ አካባቢ፣ ንጹሕ እና ዘመናዊ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የተግባቡ እና የተዋቡ የግንባታ መልኮች አዲስ አበባን እየቀየሯት ነው” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እናደርጋታለን ማለታቸውን አስታውሰው÷ “ቃል በተግባር እየተፈጸመ መሆኑን ትናንት ባደረግነው ጉብኝት አረጋግጠናል” ብለዋል።

ቃልን በተግባር ለመቀየር ለተሳተፉ አመራሮች፣ ሌት ተቀን ሳይደክሙ ለፈፀሙ ሙያተኞች እና ሰራተኞች እንዲሁም ተግባሩን በመደገፍ ህንፃቸውን እና መኖሪያቸውን በራሳቸው ተነሳሽነት ላሳመሩ እና ለደገፉ ባለሀብቶች እና ነዋሪዎች ምስጋና እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል፡፡

“በሥፍራው የነበረው ሕዝብ በድንገት ወጥቶ ላሳየን ፍቅር እና ክብር፣ ለሰጠውም ምስክርነት እናመሰግናለን“ ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.