Fana: At a Speed of Life!

የሲንጋፖር አየር መንገድ በበረራ ላይ ሳለ በተከሰተው መናወጥ ለተጎዱ መንገደኞች ካሳ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲንጋፖር አየር መንገድ በበረራ ላይ ሳለ ተከስቶ በነበረው የከባድ መናወጥ አደጋ ለተጎዱ መንገደኞች ከ10 ሺህ እስከ 25 ሺህ ዶላር ካሳ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ቦይንግ 777-300 ኢ አር የተሰኘው የሲንጋፖር አውሮፕላን 221 መንገደኞችን እና 18 የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ከለንደን ሄትሮው ተነስቶ ሲንጋፖር ቻንጊ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ አቅዶ በመጓዝ ላይ ሳለ በተከሰተ ከባድ መናወጥ ታይላንድ ማረፉ ይታወሳል፡፡

ክስተቱን ተከትሎም አንድ የ73 ዓመት አዛውንት ሕይወት ሲያልፍ÷ ከ100 የሚበልጡ መንገደኞች እና ሠራተኞች ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎም አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ÷ ከባድ ጉዳት ላጋጠማቸው ተጓዦች 25 ሺህ ዶላር እንዲሁም ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው 10 ሺህ ዶላር መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ይህም መንገደኞቹ የሚያገኙት የመጨረሻ ካሳ መሆኑን ጠቅሶ ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.