Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል መንግሥት ግዥ እና ንብረት አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት ግዥ እና ንብረት አሥተዳደር አዋጅን አጽድቋል፡፡

አዋጅ ከዚህ በፊት በመንግሥት ግዥና ንብረት አሥተዳደር ሂደትና ትግበራ ወቅት በአፈጻጸም ሲያጋጥሙ የነበሩና ለመልካም አሥተዳደር ችግር ምክንያት የሆኑ የአሠራር ጉድለቶችን ለማረም እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ወጥ የሆነ የግዥ ማዕቀፍን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ ዘርፉን ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ማራመድ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ማካተቱም ተጠቅሷል፡፡

የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች በመንግሥት ግዥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማበረታታት ሕጉን ማሻሻል ማስፈለጉም ተጠቁሟል፡፡

በተለያዩ መድረኮች የተገኙ ግብዓቶችን መሠረት በማድረግ በአዋጁ ላይ በማሻሻያነት እንዲካተቱ በማድረግ የውሳኔ ሐሳብ ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥራ መከናወኑን በምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

በየሻምበል ምኅረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.