Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መፅሃፍ ይፋ ሆነ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መፅሃፍ ይፋ ሆኗል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰብሳቢነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን አፈፃፀም በጥልቀት በመመልከት ማካሄድ ጀምሯል።

ከግምገማ መድረኩ በተጓዳኝ ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መፅሃፍ ይፋ ሆኗል።

ይህ መፅሃፍ በተጠቀሰው ዘመን የተላለፉ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በዝርዝር ያመለክታል መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል የሚያከናወነው የመሰነድ ተግባር አንዱ የሆነው ይህ መፅሃፍ ለታሪክ ስነዳ እና መረጃውን ለሚሹ ሁሉ ጠቃሚ የሆነ የሰነድ ዝግጅት ስራ አካል መሆኑም ተገልጿል።

ዛሬ ይፋ የሆነው መፅሃፍ ውስን ቅጂዎች ለፌደራል እና ለክልል ተቋማት የሚሰራጩ ሲሆን÷ መረጃውን ለሚፈልጉ ሁሉ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረገጽ ላይ የሚጫን ይሆናል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.