Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን በመጠለያ ካምፕ  ከመተንፈሻ አካላት ችግር  ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው- የዓለም የጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 9 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ሱዳን ቤንቶኡ በተባለ የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ ከመተንፈሻ አካላት ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ ።
 
በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በነዳጅ ሀብት በበለጸገችው የአንድነት ግዛት የሚገኘው ይህ ካምፕ የሚመራው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ቅርንጫፍ መሆኑ ተነግሯል።
 
በአሁኑ ወቅት በካምፑ ውስጥ 111 ሺህ 766 ሰዎች የሚገኙበት ሲሆን÷ በ2013 በመንግስት እና በአማ ጽያኑ ወታደሮች መካከል በተደረገው ጦርነት ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ትተው የተፈናቀሉ ናቸው ተብሏል።
 
የዓለም የጤና ድርጅት የስራ ሀላፊ ጆሴፍ ዋማላ በዋና ከተማዋ ጁባ ለሪፖርተሮች እንደገለጹት÷ በአሁኑ ሰዓት በካምፑ ያሉ ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት በወረርሽኙ የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑን አስታውቀዋል።
 
ሃላፊው አያይዘውም በተፈናቃዮች መጠለያ የተከሰተው ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተዛመደው ሞት ከኮቪድ -19 ጋር የተያያዘ ይሁን ወይም በሌላ ህመም ምክንያት ለማወቅ አሁንም ምርመራ እያደረግን ነው ብለዋል።
 
ደቡብ ሱዳን እስካሁን ድረስ 1 ሺህ 693 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 27 የሚሆኑት ደግሞ በወረርሽኙ ሳቢያ ለህልፈት ሲዳረጉ 49 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
 
ምንጭ፡-ቢቢሲ
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.