Fana: At a Speed of Life!

የሚዲያና ኪነጥበብ ባለሙያዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከሉ ሥራ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚዲያና ኪነጥበብ ባለሙያዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከሉ ሥራ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለፁ።

ዛሬ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የስራ ሀላፊዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ያሉበት ብሄራዊ የሚዲያና ኪነጥበባት ግብረኃይል፣ የጤና፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴሮች የስራ ሀላፊዎች የተገኙበት ቡድን በቦሌ ሚካኤል አካባቢ የችግኝ ተከላ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙት አቶ ንጉሱ ጥላሁን የሚዲያ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ የኮቪድ-19 ወረርሽን ለመግታት ጥሩ ስራ እያከናወኑ መሆናቸውን አንስተዋል።

ይህ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት እየከፋ መምጣቱን በመጠቆም ከቀደመው በበለጠ እነዚህ ባለሙያዎች ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ለዚህ ቫይረስ ወረርሽኝ በምንም መልኩ እጅ መስጠት እንደማይግባም ነው የጠቆሙት።

ሰሞኑን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የዋና መስሪያ ቤት እና የክልል ኤፍ ኤም ጣቢያዎች የስራ ሀላፊዎች እና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሚገኙባቸው ከተሞች በመዘዋወር ህብረተሰቡ ከቫይረሱ ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥንቃቄ እንዲያሳድግ የቅስቀሳ ስራ ሲያከነውኑ መቆየታቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.