Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ8 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ8 ሚሊየን መሻገሩ ተገለፀ።

የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ 8 ሚሊየን 34 ሺህ 461 የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን 3 ሚሊየን 875 ሺህ 339 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ፤ 436 ሺህ 901 ሰዎች ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

አሜሪካ ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር በመያዝ ቀዳሚ ስትሆን፥ በሀገሪቱ 2 ሚሊየን 114 ሺህ 26 ሺህ ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 576 ሺህ 334 ሰዎች አገግመው፤ የ116 ሺህ 127 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ብራዚል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ፤ እስካሁንም በሀገሪቱ በ888 ሺህ 271 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘ ሲሆን፥ በቫርሱ ምክንያትም የ43 ሺህ 957 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በሩሲያም 536 ሺህ 484 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ ህንድ 343 ሺህ 91 ሰዎች እንዲሁም ብሪታኒያ 298 ሺህ 315 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሁንም በዓለም ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ዳግም ሊያገረሽ ይችላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፥ በዓለም ላይ በየእለቱ ከ100 ሺህ በላይ ቫይረሱ እየተገኘባቸው በመሆኑ አሁንም ጥንቃቄዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አሳስበዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.