Fana: At a Speed of Life!

 በመዲናዋ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ።

ኢንጂነር  ታከለ ኡማ በሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ቀነኒ ሁንዴ መኖሪያ ቤት በመገኘት የቤት እድሳት መርሀግብሩን አስጀምረዋል።

በየአካባቢው የሚገኙ ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካማዎች መኖሪያ ቤታቸው የሚታደስ ሲሆን÷በመኖሪያ ቤት እድሳቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችና የተለያዩ አካላት የሚሳተፉ ይሆናል ነው የተባለው።

ከቤት እድሳት መርሀ ግብር በተጨማሪም “አንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው” እርስ በእርስ የመደጋገፍ መርሀግብር በይፋ ይጀመራል።

በመርሀ ግብሩ እያንዳንዱ ቤተሰብ በአቅራቢያው ላለ  የኑሮ አቅሙ ደከም ላለ ቤተሰብ ድጋፍ የሚያደርግበትና ያለውን የሚያካፍልበት ነው ተብሏል።

“በአንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው” መርሀግብር የከተማዋ ነዋሪዎች፣በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ታዋቂ ግለሰቦች፣የከተማዋ ባለሀብቶችና የከተማዋ አመራሮች እንደሚሳተፉ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.