Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መከላከል እስካሁን የ19 ቢሊየን ብር ድጋፍ ማድርጋቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ ለኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እስካሁን የ19 ቢሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃ፥ የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ቀስው ወቅት ለኢትዮጵያ አጋርነታቸውን አሳይተዋል ብሏል።

በዚህም የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ ለኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እስካሁን የ487 ሚሊየን ዩሮ ወይም የ19 ቢሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቋል።

የገንዘብ ድጋፉም የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት ለማጠናከር፣ የለይቶ ማቆያ (ኩዋራንቲን) ለማዘጋጀት፣ ለማህበራዊ ደህንነት ማጠናከሪያ እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍ የሚውል መሆኑንም ህብረቱ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እስካሁን የ60 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውቋል።

የገንዘብ ድጋፉም በድንበር አካባቢ የመሰረት ልማቶችን ለማሟላት፣ ቀጣይነት ላለው የጤና አገልግሎት፣ እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ የንግድ ሰንሰለት ለመፍጠር እና ለኮሮና ቫይረስ የጤና ምላሽ ዲጂታል መፍትሄን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑንም አስታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.