Fana: At a Speed of Life!

ሳይጠናቀቁ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ሲሰራ መቆየቱን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሳይጠናቀቁ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ሲሰራ መቆየቱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
 
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ረጅም ዓመታትን ያሰቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ከለውጡ በኋላ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲካሄድ መቆቱን ገልፀዋል።
 
ፕሮጀክቶቹ በምን ምክንያት እንደተጓተቱና መፍትሄውስ በሚለው ላይ የተለየና ዝርዝር ጥናት ተካሂዶ ለማጠናቀቅ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።
 
ለውጡ ህዝብ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳቸው የቆዩ ጥያቄዎችን መመለስ ስላለበት እና መንግስትንም ለሌላ ወጪ የሚዳርጉ በመሆናቸው ለማጠናቀቅ ርብርብ ተደርጓል ብለዋል።
 
በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩትን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶችም ከዛሬ ጀምሮ መመረቅ ይጀምራሉ ተብሏል።
 
ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የአትሌቲክስ ማእከላት፣ የመስኖ ፕሮጀክቶች የውሃ ፕሮጀክቶች እና የመንገድ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙበትም ተገልጿል።
 
ከነዚህ መካከል በ2002 ዓ.ም የተጀመሩና ተጠናቀው አሁን ለምርቃት ዝግጁ የሆኑ እንዳሉም የቢሮ ኃላፊው አቶ ጌታቸው ባልቻ ተናግረዋል።

 

በሀብታሙ ተክለስላሴ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.