Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ኢትዮጵያ የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 9 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎችና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል  የጋራ ግብረ ኃይል አቋቋሙ።

በምስራቅ ኢትዮጵያ አዋሳኝ የሆኑ የሱማሌ ክልል፣ ሐረሪ ክልል ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የጤና አመራሮች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና በድንበር አከባቢ የሚታየውን ተግዳሮቶች ለመፍታት ተስማምተዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በተገኙበት ዛሬ በድሬደዋ ከተማ አመራሮቹ ውይይት ከደረጉ በኋላ የጋራ ግብረ- ኃይሉን አቋቁመዋል።

በወቅቱም “የተጋረጠብንን ፈተና ለማሸነፍ በጋራ መቆም ይገባል”ተብሏል

የጋራ ግብረ ኃይሉ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ በተለይም በድንበር አከባቢ የሚገኙ ኳራንቲንና ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ላይ የተለዩ ክፍተቶችን በጋራ ለመፍታት መስማማታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.