Fana: At a Speed of Life!

ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ 87 ሰዎች ከሚሊኒየም ማገገሚያ ማዕከል ወጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ስር በሚገኘው የሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ከኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ያገገሙ 87 ሰዎች ከማዕከሉ መውጣታቸው ተገለጸ።

የማዕከሉ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ ÷ በአሁኑ ወቅት በማዕከሉ ውስጥ 656 ኮሮናቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ከነዚህ ውስጥ 157 ሰዎች የመጀመሪያ የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከኮሮናቫይረስ ማገገማቸውን (ኔጋቲቭ) ያሳየ መሆኑን ገልጸው÷87 ሰዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ አገግመው ዛሬ ከማዕከሉ እንዲወጡ መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሆኖ ህሙማንን መቀበል የጀመረው ከግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑ ይታወሳል።

ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል ሲሆን የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎች አሉት።

በተጓዳኝም ከማዕከሉ የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጥቷል ።

በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ እስከ ትናንትናው ዕለት 620 ሰዎች ማገገማቸው ይታወቃል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.