Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ኢንስቲትዩቱን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 9 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የኢትዮጵ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትን ጎበኘ።

የቦርዱ ጉብኝት የኢንስቲትዩቱን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችና ምላሽ ማስተባበሪ ማዕከል ከኮቪድ ቫይረስ ወረርሺኝ ጋር ተያይዞ ያለውን የኢንስቲትዩቱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለመገምገም ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከቦርዱ አባላት ጋር ስለቫይረሱ ወረርሽኝ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ሰፊ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

አቶ ዘውዱ አሰፋ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪ ማዕከል ምክትል ሃላፊ÷ የቡድኖቹ አደረጃጀትና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በዝርዝር ለቦርዱ አባላት ገለጻ አድርገዋል፡፡

በወቅቱም ዶክተር ኤባ አባተ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ÷በሽታው በሃገራችን ከመከሰቱ በፊት የነበሩትን የቅድመ ጥንቃቄ እና በሽታው ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የተሰሩ የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን እንዲሁም አጠቃላይ አለም አቀፍ መረጃዎችን ጭምር በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

ላቦራቶሪን አስመልክቶም በመጀመሪያ በ24 ሰዓት በሃገር ደረጃ መመርመር የሚቻለው 33 ናሙናዎችን ብቻ እንደነበረና በአሁኑ ሰዓት 8 ሺ ናሙናዎችን መመርመር መቻሉንና በቀጣይ በ24 ሰዓት ውስጥ 14 ሺ ናሙናዎችን መመርመር እንዲቻል ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ጥያቄዎች ከቦርዱ አባላት የተነሱ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሰፊ ማብርሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ከተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር ያለው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ የሚታዩት የተለያዩ የግብአት ክፍተቶች ከሚመለከተው አካላት ጋር በመወያየት መፍታት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ከዚያም ባለፈ ለሕብረተሰቡ የሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መጠናከር እና  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ቤት ለቤት የምርመራ ስራ መካሄድ  አለባቸው በሚሉና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረሱን ከኢንስቲቲዩቱ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.