Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር የባቡር ካፒቴኖች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 9፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ለመጀመሪያ ግዜ የባቡር ካፒቴኖች አስመረቀ።

የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ላለፉት 6 ወራት በሃገረ ቻይና ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 34 ኢትዮጵያውያንን የአዲስ አበባ- ጅቡቲ የኤሌክትሪክ የባቡር ካፒቴኖችን ለመጀመሪያ ግዜ አስመረቀ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ÷ተመራቂዎች ወደ ስራ ሲገቡ ህዘባቸውን በታማኝነት እንደሚያገለግሉ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም ሚኒስቴሩ በዘርፉ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሸግግርን እውን ለማድረግ እየሠራ  ነው ማለታቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.