Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

በሀዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው አስቸኳይ ጉባዔ ላይም የምክር ቤቱ አባላት በአራት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የምክር ቤት አፌ ጉባኤ ወይዘሮ ሄሌን ደበበ በጉባዔው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፥ ምክር ቤቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርትይመለከታል።

እንዲሁም ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ላይ እና በአዲስ መዋቅር ለመደራጀት የቀረበ ጥያቄ ምላሽ እና የውሳኔ ሀሳብ ሪፖርት እንደሚመለከትም አስታውቅዋል።

በመጨረሻም የስልጣን ርክክብ ማድረግ ከአስቸኳይ ጉቤዎች አጀንዳዎች ውስጥ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት የደቡብ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ወረርሽኝ መከላከል እና ቁጥጥር ስራዎች አስመልክቶ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ በአቶ አቅናው ካውዛ አማካኝነት የቀረበለትን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.