Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ አፍሪካን በመወከል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነትን አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ አፍሪካን በመወከል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነትን አገኘች።

አፍሪካን ወክሎ የምክር ቤቱን ተለዋጭ አባልነት ለማግኘት በተደረገው ምርጫ ኬንያ ጂቡቲን በድምጽ ብልጫ አሸንፋለች።

ለአባልነት በተሰጠው ድምጽ ኬንያ 129 ድምጽ ስታገኝ ጂቡቲ ደግሞ 62 ድምጽ አግኝታለች።

ማሸነፏን ተከትሎም ኬንያ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ የነበራት ደቡብ አፍሪካን የምትተካ ይሆናል።

ሁለቱ ሃገራት በመጀመሪያው ዙር ድምጽ አሰጣጥ ላይ አሸናፊ ለመሆን የሚያስፈልገውን 2/3 ድምጽ ማግኘት አልቻሉም ነበር።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሃገራቸው ማሸነፏን “ሃገሪቱ በልማት አጋርነት እያመጣች ያለው እድገት ማሳያ ነው” ብለውታል።

ኬንያ በምክር ቤቱ ቆይታዋም የአፍሪካን ተሰሚነትና ድምጽ መጨመር እንዲሁም ለጉባኤው ምርጫ ስትንቀሳቀስበት የነበረውን ባለ 10 ነጥብ አጀንዳ ታስተዋውቃለች ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.