Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ስኬት ለአፍሪካ ስኬት ቁልፍ መሆኑን የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ስኬት ለአፍሪካ ስኬት ቁልፍ መሆኑን የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ባጸደቀው 250 ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት ዙሪያ መወያየታቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፈረዋል።

በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር የምታደርገውን ውይይት ዘላቂ ማድረግ እንደሚገባት አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያና ጎረቤቶቿ በሚጋሩት የውሃ ሃብት ዙሪያ ትብብር ማድረግ እንደሚገባቸውም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ250 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት ትናንት መፈራረማቸው ይታወሳል።

ከዚህ ውስጥ 125 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በብድር መልክ ቀሪው 125 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በድጋፍ መልክ የሚለቀቅ ነው።

የገንዘብ ድጋፍና የብድር ስምምነቱ በመተግበር ላይ ላለው የኢትዮጵያ እድገትና የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት መርሃ ግብር ፖሊሲ ማስፈፀሚያ እንደሚውል ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ሚና በማስፋፋት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ እና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚረዳ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያፋጥን መሆኑም ተመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.