Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት የኦክሲጅን እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም መወሰኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡

በዚህም በህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድን እና በጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት በተሰጠ ምክረ ሀሳብ መሰረት፥ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.