Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በሴቶች ብቻ የሚካሄድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በሴቶች ብቻ የሚካሄድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ ተጀመረ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ ሴት አመራሮች ተገኝተዋል።

መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ችግኝ መትከል የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ማህበራዊ ችግሮቻቸውን ለማቃለል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

የአቮካዶ ፣የማንጎና የዘይቱን ችግኝ ዝርያዎች መትከል ደግሞ ከዘርፉ ሴቶች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እድል በተሻለ ያሳድገዋል ብለዋል።

የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙና አህመድ በበኩላቸው በክልሉ ዘንድሮ ለመትከል ከታሰበው 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 40 በመቶውን የሚተክሉት ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አለምፀሀይ ሽፈራው ቢሾፍቱ ከተማ ቀድሞውንም በአረንጓዴ ልማት ስራ ላይ ሰፋፊ ስራዎችን ስትሰራ መቆየቷን አስታውሰዋል፡፡

ይህንኑ በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ2 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከልና ለመንከባከብ በትኩረት እንደሚሰራም አስረድተዋል።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት አመራሮች በከተማዋ በዜግነት አገልግሎት መርሃ ግብር የሚጠገኑ የአቅመ ደካማ ዜጎችን ቤት አስጀምረዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.