Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 116 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 809 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 116 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ3 እስከ 78 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ከዚህ ውስጥ 76 ወንዶች እና 40 ሴቶች ናቸው። 101 አዲስ አበባ፣ 6 ኦሮሚያ ክልል፣ 4 ደቡብ ክልል፣ 1 ጋምቤላ ክልል፣ 1 አማራ ክልል፣ 1 ትግራይ ክልል፣ 1 ድሬዳዋ እንዲሁም አፋር ክልል 1 ሰው ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በተያያዘ በትናንትናው እለት የ7 ሰዎች (4 ከአዲስ አበባ፣ 1 ከሶማሌ፣ 1 ከድሬዳዋ እንዲሁም 1 ከሐረሪ ክልል) ህይወት አልፏል።
ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 72 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 93 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 27 ደርሷል ነው የተባለው።

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ207 ሺህ 23 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሺህ 70 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.