Fana: At a Speed of Life!

የሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።

በዚህ ወቅትም በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ውጤታማ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

የሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀኔራል መሐመድ ሐምዳን ባለፈው ረቡዕ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

በቆይታቸውም ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.