Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ስኬታማ እንደነበር ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ።

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ግብዣ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉበኘት ያደረጉት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው በሀገሪቱ እየተካሄዱ ያሉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይም ከጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር መክረዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጉበኝትቸውን ዛሬ አጠናቀው ሲመለሱ በካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጉብኝታቸው ስኬታማ እንደነበር ነው የተናገሩት።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በድንበር ጉዳይ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት እና በአቢዬ ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በጉበኝታቸው በኢትዮጵያ በመንገድ፣ በባቡር መስመር ዝርጋታ፣ በኢንዱስትሪ እና ግብርና ልማት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎች ለመመልከት መቻላቸውን ነው የተናገሩት።

በዚሁ ወቅትም ከጅቡቲ አዲስ አበባ የተዘረጋው የባቡር መስመር ቀጥሎ ከካርቱም እና ፖርት ሱዳን ጋር በሚገናኝበት ሁኔታ ላይ መክረናልም ነው ያሉት።

በመሆኑም ወጣት የሱዳን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ እድሎች እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.