Fana: At a Speed of Life!

ግብጽ በድርድር ሂደት ላይ ያለውን የግድቡን ጉዳይ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን እንደማትቀበል ሱዳን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብጽ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ በድርድር ሂደት ላይ እያለ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን እንደማትቀበል ሱዳን ገለፀች።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ኡመር ቀመረዲን ከቢቢሲ አረብኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት ብትጀምር ሱዳን ከኢትዮጽያ ጋር ወደ ግጭት እንደማትገባ ግልፅ አድርገዋል።

ሀገራቸው ችግሩ በዲፕሎማሲ መንገድ ብቻ እንዲፈታ እንደምትሰራም ነው የተናገሩት።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው አርብ ሀገራቸው ጉዳዩን ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን መግለፃቸው ታወሳል።

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የመጀመሪያ የውሃ ሙሌትን በሚቀጥለው ወር ለመጀመር የማንም ፈቃድ እንደማያስፈልጋት አስታውቃለች።

በዚህ ክረምት የውሃ ሙሌቱን ለማስጀምር በሚያስችላት ዝግጅት ላይም ትገኛለች ።

ሰሞኑን ሶስቱ ሀገራት በግድቡ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት ላይ አንዳች ስምምነት ላይ ለመድረስ በቪዲዮ ኮንፍረንስ ለበርካታ ቀናት ሲደራደሩ የቆዩ ሲሆን፥ በመሰረታው የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን፥ ህግ ሆኖ ለመውጣት በሚያስችሉ የህግ ጉዳዮች ላይ ግን እንደሚቀራቸው ነበር የተገለፀው ።

በእስካሁኑ የድርድር ሂደት ላይ ሱዳን ተጨማሪ ምክር እንደምትፈለግ መግለጿን ተከትሎ ድርድሩ ከዚያ በኋላ እንደሚቀጥል በመስማማት ነበር የተለያዩት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.