Fana: At a Speed of Life!

ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፉ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት በባህርዳር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፉ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት በባህርዳር እየተካሄደ ነው።

በሥነ ሥርዓቱ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ግቢ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የተጀመረ ሲሆን ለመሪዎቹ የመታሰቢያ ሃውልት መሠረትም ተቀምጧል፡፡

የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዝክረ ሰማዕታት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርም ማካሄዳቸውን አብመድ ዘግቧል።

በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልሉ ምክር ቤት አፊ ጉባኤ ወርቅ ሰሞ ማሞ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተሳተፉበት ዝክረ ሰኔ 15 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

በመርሀግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እንዲሁም የተለያዩ አመራሮችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.