Fana: At a Speed of Life!

የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች የችግኝ ተከላ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከፍትኛ አመራሮች በእዲሱ የመከላከያ ሚኒስቴር ህንፃ ተገኝተው የችግኝ ተከላ ስነስርአት እካሄደዋል።

በስነ ስርአቱ ላይ የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የሃይሎችና የዕዝ አዛዦች እንዲሁም ጄኔራል መኮንኖችና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ መርሃ ግብር በይፋ መጀመሩን አስታውቀዋል።

በዘንድሮ አመት በመላው ሰራዊታችን 5 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉና እንክብካቤ እንደሚደረግላቸውም አብራርተዋል።

የችግኝ ተከላው የተጀመረበት አዲሱ የመከላከያ ሚኒስቴር ህንፃ ዘመናዊና ግንባታው ሲጠናቀቅም ለህዝብ ክፍት የሆነ ሙዚየም የመሳሰሉ በርካታ አገልግሎት መስጫዎች እንዳሉት መገለጹን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.