Fana: At a Speed of Life!

ለበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሜዳ ቴኒስ ላይ የተሳተፈው ዲሚትሮቭ የኮሮና ቫይረስ ተገኘበት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ግሪጎር ዲሚትሮቭ ለበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀ ጨዋታ ላይ ከተሳተፈ በኋላ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ተነገረ።

በወንዶች የሜዳ ቴኒስ ቀዳሚ በሆነው ኖቫክ ጃኮቪች አስተባባሪነት በተዘጋጀው የበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ላይ ከተሳተፈ በኋላ ነው ቡልጋራዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ቫይረሱ የተገኘበት።

የበጎ አድራጎት ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኖቫክ ጃኮቪችም ተገቢው ጥንቃቄ ያልተደረገበት ዝግጅት በማዘጋጀቱ ወቀሳ እየቀረበበት ይገኛል።

ይህ ዝግጅትም ዲሚትሮቭ ቫይረሱ ከተገኘበት በኋላ መሰረዙ ተነግሯል።

ዲሚትሮቭ በኢንስታግራም ገፁ ለአድናቂዎቹ ባስተላለፈው መልዕክት ጎደኞቼ እና አድናቂዎቼ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘብኝ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ ብሏል።

ላስከተልኩት ማንኛውም ጎጂ ነገር ይቅርታ እጠይቃለሁ ያለው ተጫዋቹ ለድጋፋችሁም አመሰግናለሁ ሲል ለአድናቂዎቹ መልዕክት ማስተላለፉን አልጀዚራ የዘገበው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.