Fana: At a Speed of Life!

የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ ከዛሬ ጀምሮ መካሄድ መጀመሩን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ የቅኝትና የዳሰሳ ምርመራው እስከ ሀምሌ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ አስታውቋል።

ምርመራው ከሰውነት ከ3 እስከ 5 ሚሊ ሊትር የደም ናሙና በመውሰድ የሚደረግ ኮቪድ-19ኝን ለመካላከል እና ለመቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ተብሏል።

ይህ የቅኝት ዳሰሳው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለማወቅ በሚረዳ መልኩ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ይካሄዳልም ነው ያለው።

በመሆኑም ህብረተሰቡ፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለትግበራው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪውን አቅርቧል።
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻ ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁም ጠይቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.