Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለውጭ  ዜጎች  ቪዛ  እንዳይሰጥ መመሪያ አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  እስከ ፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ ድረስ ለውጭ ዜጎች አዲስ  ቪዛና  ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳሰጥ መመሪያ አስተላለፉ።

መመሪያው ተግባራዊ ሲፈደረግ በቴክኖሎጂ ዘርፉ ከፍተኛ ስልጠኛ ያላቸው፣ የከፍተኛ ኩባንያ ስራ አስፈጻሚዎች፣ከግብርና ውጪ ባሉ ሙያዎች ላይ የሚሰማሩ የጉልበት ሰራተኞች  እንዲሁም የቤት ውስጥ ሰራተኞች ላይ ተጽዕኖ ያሳድርባቸዋል ተብሏል፡፡

ከዚያም ባለፈ መመሪያው ተግባራዊ ሲሆን በኤጀንሲዎች እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች  ውስጥ የሚሰሩ  ቁልፍ ሠራተኞችን ላይም ተጽእኖ ይፈጥራል ተብሏል።

ነገር ግን ነባር ቪዛ ያላቸው ሰዎችን መመሪያው እንደማያጠቃልልም ነው የተገለጸው።

እርምጃው  በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በኢኮኖሚ ለተጎዱ አሜሪካውያን የስራ እድል  ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ከነጩ  ቤተመንግስት የወጣው መረጃ ያመላክታል ።

አስተዳደሩ ለሪፖርተሮች ባቀረበው አጭር መግለጫም÷የተላለፈው መመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ  ወደ 525 ሺህ ሰዎችላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ  እንደሚችል  ጠቅሷል።

ከዚያም ባለፈ አዲሱ መመሪያ 170 ሺህ የሚሆኑ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ  ለማግኘት የሚፈልጉ የውጭ አገር ዜጎችን ያግዳል ነው የተባለው

ነገር ግን ተቺዎች የአሜሪካ መንግስት  ወረርሽኙን እንደምክንያት በመጠቀም የኢሚግሬሽን ህጎችን  በማጥበቅ ላይ ነው ሲሉ ተችተዋል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.