Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ በክፍለ ከተማው በነበረው ቆይታ ከ47 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 16 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሕዳሴው ግድብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በነበረው  የገቢ ማሰባሰቢያ ቆይታ ከ47 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል።

የህዳሴ ግድብ ዋንጫው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በነበረው የ20 ቀናት ቆይታ   32 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ÷ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ ቃል የተገባ መሆኑ ተገልጿል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተረከበውን የህዳሴ ግድብ ዋንጫም በዛሬው ዕለት  ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እንደሚያስረክብ ተገልጿል።

የክፍለከተማው ነዋሪዎችም ከዚህ በኋላም ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በጸጋዬ ንጉስ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.