Fana: At a Speed of Life!

ለአዳዲስ አምባሳደሮች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት እንዲወክሉ ለተሾሙት አዳዲስ አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የሎጀስቲክስ አሰራር የተመለከተ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ አምባሳደሮች ስለ አገራቸው አጠቃላይ የሎጂስቲክስ አሰራር በቂ መረጃ እንዲኖሯቸው ሥልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል።

በዚህም  በተወከሉበት አገር የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም በአግባቡ ለማስጠበቅ እንዲችሉ መሰል ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን  ገልጸዋል።

ስልጠናው በኢትዮጵያ ማሪታይም ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን አበራ አማካኝነት በመሰጠት ላይ ሲሆን÷ በዋናነትም የአገር አቀፍ ሎጅስቲክስ ስርዓት፣ የሎጀስተክስ ፖሊሰ እና ሰማያዊ ኢኮኖሚ በሚሉ ርዕሶች ላይ  አትኩሮት መሰጠቱ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ የሎጅስቲክስ አሰራር ጋር በተያያዘ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰራር ጋር በተያያዘ ከመስሪያ ቤቶቹ በመጡ ከፍተኛ አመራሮች አማካኝነት መሰል ስልጠና በቀጣይነት እንደሚሰጥ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.