Fana: At a Speed of Life!

የብሮድካስት ባለስልጣን ለሶስት የሬድዮ ጣብያዎች ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 16 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሶስት አዳዲስ የሬድዮ ጣብያዎች ፈቃድ ሰጠ።

ፈቃድ ያገኙት ኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን፣ ትርታ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና አዲስ ኦንላይን የሚዲያና የግብይት ስራዎች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር  መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ÷ በአገሪቱ የተለያየ ሃሳብና አመለካከት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን እንዲበራከቱ ይፈለጋል ብለዋል።

ይህም በተለይ  ህብረተሰቡ የመረጃ አማራጮችን ከማስፋቱ ባሻገር በተለያዩ አቅጣጫዎች ከጣቢያዎቹ ትምህርት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ትልቅ ደርሻ አለው ብለዋል።

አያይዘውም ፈቃድ የተሰጣቸው ጣቢያዎች በተሰጣቸው ሃላፊነት መሰረት ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ከዚያም ባለፈ ራሳቸውን ከየትኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ በማድረግም አገራዊ፣ ህዝባዊና ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

ባለስልጣኑ የሚዲያ ልማትን ማሳደግና ማስፋፋት ላይ በትኩረት የሚሰራ ሲሆን ከተሰጣቸው ሃላፊነት ውጪ በሚሰሩና ህዝብን ከህዝብ እና ከመንግስት ጋር የሚያጋጩ ስራዎችን በሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከ72 በላይ የማህበረሰብ፣ የግል (የንግድ) እና የህዝብ የሬድዮ ጣብያዎች ሲኖሩ ÷37 የቴሌቭዥን ጣቢያዎች  መኖራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.