Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ኮንግረስ የብላክ ኮከስ ግድቡን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ባለስርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ሰላማዊ እልባት ለመስጠት እንዲሰራ ጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ኮንግረስ የብላክ ኮከስ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቱ የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ሰላማዊ እልባት ለመስጠት እንዲሰራ ጠየቀ።

የኮንግረሱ የጥቁር አሜሪካውያን አባላት ስብስብ የሆነው ብላክ ኮከስ የአፍሪካ ህብረት አሁን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ቁልፍ ሚና እንዳለው አስታውቋል።

ይህንን ሚናውን ተጠቅሞ ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ቢንቀሳቀስ ኮከሱ ድጋፉን እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

በመግለጫቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፍሪካ ትልቁ የውሃ ሀይል አመንጪ በመሆን በአህጉሪቱ ላይ አወንታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረው አስታውቋል።

በቀጥታ የወንዙን ፍሰት በማሻሻል በሀይል አቅርቦት እና በምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋልም ብሏል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.