Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ምግብ ፕሮግራምና ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ ጥምረት ፈጠሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ በጋራ ለመስራት ጥምረት መፍጠራቸው ተገለፀ።

ለ3 ዓመታት የሚቆየው ጥምረቱ መንግስትን በማገዝ በኢትዮጵያ በህፃናትና በእናቶች ላይ የሚያጋጥመውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመቅረፍ እና የትምህርት ቤት ምገባን ለማገዝ እንደሆነም ተነግሯል።

በያዝነው ዓመት በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ህፃናት እና 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ነብሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች በድምሩ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች ከተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን፣ በበረሃ አንበጣ መንጋ ወረርሽኝ እንዲሁም ጎርፍ እና ድርቅን በመሳሰሉ ተፈጥሯው አደጋዎች አማካኝነት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋላጭነቱ የበለጠ ከፍ ሊል እንደሚችልም ተነግሯል።

ዩኒሴፍና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋራ ይፋ ያደረጉት መርሃ ግብርም መንግስትን በማገዝ እነዚህ ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

እንዲሁም እንደ አውሮፓውያኑ 2030 በኢትዮጵያ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ችግርን ከ10 በመቶ ወደ 3 በመቶ ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ተቋማት ጥምረት ፈጥረው ይፋ ያደረጉት ድጋፍም በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሶማሌ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 100 ወረዳዎች የሚተገበር መሆኑም ታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.